ዋና ፕሮግራሞች
የጌልማ ዋና የልማት ፕሮግራሞች እና በእያንዳንዱ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች
ትምህርት
የትምህርት ተደራሽነት በዞኑ ከማረጋገጥ አኳያ ትምህርት ለሁሉም ዜጐች አንዲደርስ ልማት ማህበሩ ለህበረተሰቡ ትምህርት ቤቶችን የገነባ ሲሆን በሀገሪቱ ትምህርት ለማስፋፋት ከተቀመጠዉ አቅጣጫ አንፃር ለህብረተሰቡና ለመንግስት ወሳኝ ሚና በመጫወት ላይ የይገኛል።
ዋና ስኬቶች
35+ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል
80,000+ ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል
100+ ሚሊዮን ብር ኢንቨስት ተደርጓል
3000+ ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በዶክተሬት ድግሪ የተማሩ እና በመማር ላይ ያሉ

ጤና
የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንዲቻል የማይናቅ ሥራዎችን አከናዉኗል፡፡ ለምሳሌ ሶክቻሾባ ጤና ኬላ ግንባታ፣ ሀሮ ወላቡ ጤና ኬላ፣ ጨብቻ ጤና ኬላና ይ/ጨፌ ጤና ጣቢያ ማስፋፍያ ሥራዎች
ዋና ስኬቶች
10+ የጤና ኬላዎች ተገንብተዋል
HIV/AIDS ቁጥጥር ፕሮግራሞች
50+ ሚሊዮን ብር የጤና ፕሮጀክት ሥራዎች ተከናወኗል
የእናቶች ጤና አገልግሎት ተሠርቷል

ንጹህ ውሃ
በንጹ መጠጥ ዉሃና ሳንተሽን ሥራ አገራዊ ዕቅዶች ላይና የሚእተ አመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት ከዞኑ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ትኩረት አድርጎ የሰራ ሲሆን በዚህ ላይ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ከፍ ለማድረግ በተደረገውን ጥረት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል።
ዋና ስኬቶች
20+ የውሃ ፕሮጀክቶች ተከናውነዋል
30,500+ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል
1.3 ሚሊዮን ብር ተኢንቨስት ተደርጓል
16 አመት ዘላቂነት አላቸው

ግብርና
በዞኑ ያለዉን የተፈጥሮ ሀብት በዩኒስኮ(UNESCO) አንዴመዘገብ በዞኑ ያለዉን ተፈጥሮአዊ ሀብት ጥቅጥቅ ደን ተጥብቆ እንዲቆይ የበኩሉን አስተወጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ንብን ማርባት እና የማር ምርትን ወደ ዘመናዊ መንገድ መቀየር።
ዋና ስኬቶች
የቡና ምርት ተሻሽሏል
ዘመናዊ የንብ አርቢ ቴክኖሎጂ
የደን ጥበቃ ፕሮግራሞች
የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ

የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች
ልማት ማህበሩ በብዙ ዘርፎች ገቢ ማስገኛ ፕሮጀከቶችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ለአብነት ያህል በሀገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰልን ከቡና ቅርፊት(አሻራ) ከተለያዩ ቆሻሻዎችና ከእፅዋት የሚያመርት ፋብሪካን ገስቶ ወድ ሰራ ተገብቷል። ፋብሪካው ግንባታ የወጣዉ ወጪ 2 ሚሊዮን ብር ነዉ።
ዋና ስኬቶች
የከሰል ፋብሪካ
የመዝናኛ ማዕከል
የእርሻ ልመት ሥራ
40+ ሚሊዮን ብር ተኢንቨስት ተደርጓል

ቋንቋ እና ባህል
የጌዴኦ ህዝብ ህገ መንግስቱ ለብሔር ብሔረሰቦች ባጎናፀፈዉ መብት በመጠቀም ቋንቋውን እና ባህሉን ለማዳበር ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል። የጌዴኦፋ ቋንቋ ለማሳደግ ሥራን በማጠናከር የስነ-ጥበብ ቡድን በማደራጀት የመጀመሪያዉን የጌዴኦፋ ድክሽነሪ እና የባህል ታሪክ መጽሐፍ በማሳተም አለገልግሎት አብቅቷል::
ዋና ስኬቶች
የጌዴኦፋ መዝገበ ቃል ማሳተም እና ማከፋፈል
የታሪክ መጽሐፍ ማሳተም እና ማከፋፈል
የባህል ሙዚቃዎች ሥራዎችን ማሳተም እና ማከፋፈል