አብረን ከተባበርን
እንችላን!
የአባልነት ማዕቀፎች ለግለሰቦች፣ ለግል ድርጅቶች እና ለመንግሰት ተቋማት
የልማት ማህበሩ አባል በመሆን የለውጡ አካል ይሁኑ
የተማረ የሰው ኃይል
የትምህርት ያለፈ ሰው ኃይልን ለማሳደግ ያለው መሠረታዊ ራእይ አማካኝነት፣ ጌዴኦ ልማት ማህበር ከ26 ዓመታት በላይ ባለፈው ጊዜ ባለብዙ ደረጃ የትምህርት ድጋፍ ፕሮጄክቶችን ተግብሮ ይገኛል። ፕሮጄክቶቻችን በሁሉም ደረጃ ሊቃውንት እንዲያፈሩ በማሰብ የተዘጋጁ ናቸው
ደራሮ አዳሪ ትምህርት ቤት
በትምህርት አቅርቦት ላይ እንደ አንድ ጉልህ ምዕራፍ በሚቆጠር መልኩ፣ ደራሮ አዳሪ ትምህርት ቤት ከጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ 212 ተማሪዎችን በመቀበል በይፋ ተመርቆ የመማር ማስተማር ሥራውን ጀምሯል፡፡ ይህ ታላቅ ምዕራፍ ሊሳካ የቻለው የጌዴኦ ዞን አስተዳደር፣ የጌዴኦ ልማት ማህበር፣ የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቀድሞው የሆስቴል ማዕከል ላይ በአጭር ጊዜ መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የመመገቢያ አዳራሽ ግንባታ፣ የተጠናከረ የአጥር ግንባታ፣ የሴቶች እና ወንዶች ዶርሚተሪ ክፍሎችን ሙሉ እደሳ እንዲሁም ዘመናዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ላብራቶሪ ማቋቋምን አካቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ልማት ማህበሩ፤ ትምህርት ቤቱ ብቁ መምህራንን፣ የአስተዳደርሠራተኞች እና ለስኬታማ የመማር ማስተማር ሂደት ምቹና አበረታች አከባቢ ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ሌሎች ወሳኝ ግብዓቶች በሙሉ እንዲሟሉ አድርጓል፡፡

ሆስቴል ተማሪዎች ፕሮጀክት

የጌዴኦ ልማት ማህበር ባለፉት 26 ዓመታት እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የተማሪዎች ማደሪያ፣ ምግብ፣ የጤና አገልግሎት እና የትምህርት ክፍያን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፤ ይህም ማህበረሰቡን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት አግዟል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ድጋፍ

የጌዴኦ ልማት ማህበር በድላ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎች ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ እና ሌሎች የትምህርት ወጪዎችን በመሸፈን ያስምራል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል የማብቃት ራዕዩን እዲያሳካ አድርጎታል።
የሁለተኛ ዲግሪ ድጋፍ

ከመጀመሪያ ዲግሪ ድጋፍ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ የጌዴኦ ልማት ማህበር የማስተርስ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ በመሸፈን ድጋፍ ያደርጋል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል ለማብቃት ነው።
የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች

የጌዴኦ ልማት ማህበር በተለያዩ የአገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ በመሸፈን ያስምራል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል የማብቃት ራዕዩን ያጠናክራል።
በቅርብ ጊዜ ከተከናወኑ ፕሮጀክቶችን በጥቂቱ
በዞኑ በሚገኙ ወረዳወች እና ከተማ አስተዳደሮች ላይ ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል በጥቂቱ ይመልከቱ
የትምህርት መሰረተ ልማት
የቡሌ ከተማ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት
6 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎች እና መጸዳጃ ቤቶች ያሉት ሲሆን በአንድ ጊዜ 300 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።

የገደብ ከተማ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት
በ2023 ተጠናቀቀ እና በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በልማት ማህበሩ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ማስፋፊያ
በአጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ያለዉን የክፍል ጥበት ለመቅረፍ ማስፋፊያ አንድ ብሎክ ሕንጻ ተገንብቶ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም ርክክብ ተደርጓል።
የራጴ ወረዳ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት
የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ተከናዉኖ የካቲት 23/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎ በመስጠት ላይ ይገኛል።
የባንቆ ኦኮቶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የባንቆ ኦኮቶ 1ኛ ደረጃ ትምህት ቤት 4 ብሎክ ሕንጻ ግንበታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል
የጨለለቅቱ ከተማ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል
የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የጮርሶ ወረዳ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል
የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ጤና እና የሕክምና ተቋማት
የጪጩ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ
የወላዶችን የጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና የመውለጃ ክፍሎች ቦታ ጥበትን አንዲያስችለል ልማት ማህበሩ ለዚሁ አገልግሎት የሚዉን አንድ ብሎክ ህንጻ ገንብቶ ለአገልግሎት አብቅቷል።

የእርሻ ፕሮጀክቶች
የእርሻ ፕሮጀክቶች
የእርሻ ፕሮጀክቶች፣ በአሁኑ ወቅት ስንዴ፣ በቆሎ እና እንደ ድንች ያሉ አትክልቶችን በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የበኩሉን በመወጣት ላይ ይገኛል።


















